ስለ coronavirus (COVID-19) ወረርሽኝ ምክርና ወቅታዊ መረጃ።.
Information, updates and advice about the outbreak of coronavirus (COVID-19).
በዚህ ገጽ ላይ (On this page)

የሚያሳስብዎት ከሆነ ለኮሮና ቫይረስ/coronavirus በሆትላይን 1800 675 398 (24 ሰዓታት) መደወል።.
አስተርጓሚ ካስፈለግዎት፤ ለ TIS National በስልክ 131 450 መደወል.
እባክዎን በሶስት ዜሮ (000) ለድንገተኛ ችግር ብቻ መደወል.

ምን ማስታወስ እንደሚኖርብዎት (What you must remember)

 • የኮሮና ቫይርስ coronavirus ምልክቶች ከተሰማዎት መመርመር አለብዎት።
 • የህመም ስሜት ካለዎት፤ እቤትዎ ይቆዩ። ቤተሰብዎን አይጎብኙ ወይም ወደ ሥራ አይሂዱ።
 • እጅዎን ይታጠቡ፣ ሲያስነጥሱ ወይም ሲያስሉ አፍዎን እና አፈንጫዎን ይሸፍኑ እንዲሁም ከሌሎች ሰዎች ጋር የሚኖርዎትን የ 1.5 ሜትር የደህንነት ርቀት ይጠብቁ።
 • የሚችሉ ከሆነ እቤትዎ ሆነው መሥራትዎን ይቀጥሉ።
 • ሁኔታው ከተቀየረ ዋናው የጤና መኮንን  (Chief Health Officer)  ገደቦችን ሊለውጣቸው ይችላል።.

በቪክቶሪያ በቅርብ የወጡ መመሪያዎች (Latest restrictions in Victoria)

ከቀን 2 ሐምሌ/July ጀምሮ በቪክቶሪያ አንዳንድ አካባቢዎች የተለየ ገደብ በሥራ ላይ ይውላል።

በመላው ቪክቶሪያ ክፍለ ሃገር አቀፍ እገዳዎች

ከቀን 2 ሐምሌ/July ፡

 • የገበያ ማእከሎችና በውጭ የሚደረጉ ገበያዎች የገበያተኖቻቸውን ቁጥር መወሰን አለባቸው።
 • ከተገደቡት መንደሮች ውጭ የሚኖሩ ሰዎች ወደነዛ መንደሮች መጓዝ የሚችሉት ለአራት ምክንያቶች ብቻ ይሆናል፡
 1. ምግብ ወይም ሌላ አስፈላጊ ነገሮችን ለመግዛት
 2. እንክብካቤ ለማድረግ፣ በርህራሄ ምክንያቶች ወይም ለህክምና
 3. በውጭ ለሚደርግ የአካል እንቅስቃሴ
 4. ለሥራ ወይም ለትምህርት፣ ከቤት ሆነው መሥራት ወይም መማር ካልቻሉ

(ከታች) የተዘረዘረው  ከቀን 22 ሰኔ/June ጀምሮ ተጥሎ የነበረው እገዳ አሁንም በመላው ቪክቶሪያ ይሠራል። በተጨማሪ፡

እገዳ የተጣለባቸው ፖስት ኮዶች

ከቀን 2 ሐምሌ/ July ጀምሮ 3ኛው በቤት ውስጥ መቆየት (Stage 3 Stay at Home) ግደባ በነዚህ መንደሮች ሥራ ላይ ይውላል፡

 • 3038 – Keilor Downs, Keilor Lodge, Taylors Lakes, Watergardens
 • 3021 – Albanvale, Kealba, Kings Park, St Albans
 • 3012 – Brooklyn, Kingsville, Maidstone, Tottenham, West Footscray
 • 3042 – Airport West, Keilor Park, Niddrie, Niddrie North
 • 3064 – Craigieburn, Donnybrook, Mickleham, Roxburgh Park, Kalkallo
 • 3047 – Broadmeadows, Dallas, Jacana
 • 3060 – Fawkner
 • 3032 – Ascot Vale, Highpoint City, Maribyrnong, Travancore
 • 3046 – Glenroy, Hadfield, Oak Park
 • 3055 – Brunswick South, Brunswick West, Moonee Vale, Moreland West

and from 5 July

 • 3031 – Kensington, Flemington
 • 3051 – North Melbourne, Hotham Hill

ከቀን 2 ሐምሌ/ July ጀምሮ፣ በእነዚህ አካባቢዎች የሚኖሩ ከሆነ፣ ከቤት ሊወጡ የሚችሉባቸው ምክንያቶች አራት ብቻ ናቸው፡

 1. ምግብ ወይም ሌላ አስፈላጊ ነገሮችን ለመግዛት
 2. እንክብካቤ ለማድረግ፣ በርህራሄ ምክንያቶች ወይም ለህክምና
 3. ለአካል እንቅስቃሴ (በውጭ ለሚደረግ የአካል እንቅስቃሴ፣ ከአንድ ሌላ ሰው ጋር ብቻ ወይም ከቤተሰብ አባል ጋር)
 4. ለሥራ ወይም ለትምህርት፣ ከቤት ሆነው መሥራት ወይም መማር ካልቻሉ

እቤትዎ ጎብኝዎችን ማምጣት አይችሉም ወይም ሌሎችን፣ ለእንክብካቤ ወይም በርህራሄ ምክንያት ካልሆነ፣ መጎብኘት አይችሉም። ከላይ ከተዘረዘሩት አራት ምክንያቶች ውጭ ጉዞ ማድረግ አይችሉም።

በእነዚህ መንደሮች postcodes እንቅስቃሴዎች እና የዝግጅት ማእከሎች እገዳው በሥራ ላይ ይውላል፡

 • ሬስቶራንቶች እና ካፌዎች ተይዞ የሚሄድ ወይም በአድራሻ የሚላክ አገልግሎት መስጠት ይችላሉ
 • መጠጥ ቤቶች፣ ቡና ቤቶች እና ክለቦች ዝግ ይሆናሉ፣ ተይዞ ለሚሄድ ምግብ ወይም የአልኮል መጠጥ አገልግሎት ካልሆነ በስተቀር
 • የቁንጅና እና የግል የእንክብካቤ አገልግሎቶች ዝግ መሆን አለባቸው፣ ከፀጉር ሥራና ማስተካከያ በስተቀር
 • ቤተ መጽሐፍቶች፣ የማህበረሰብ መሰባሰቢያዎች፣ የስፖርት ማእከሎች እና የእረፍት ጊዜ ማረፊያዎች ይዘጋሉ
 • የስእል ማሳያዎች፣ ቤተ መዘክሮች፣ ታሪካዊ ቦታዎች፣ መካነ አራዊቶች፣ የውጭ መዝናኛ መናፈሻዎች እና አርኬዶች፣ የመጫወቻ ማእከሎች፣ የውስጥ እና በመኪና ውስጥ ሆኖ ሲኒማ መታያዎች፣ የትርኢት መታያ ቦታዎች፣ ቲያትር ቤቶች፤ መሰብሰቢያ አዳራሾች፣ አሪናዎች፣ እስታዲየሞች፣ ካሲኖዎች እና የቁማር ቤቶች ይዘጋሉ።
 • የውስጥ እና የውጭስፖርት መስሪያዎ፣ ጅምናስቲክ መሥሪያዎች፣ ማሰልጠኛ ቦታዎች እና መዋኛ ቦታዎች ዝግ ይሆናሉ። ውጭ የሚደረግ የግል ሥልጠና ልምምድ፣ ሁለት ተሳታፊዎች፣ አሰልጣኙን ጨምሮ፣ ይቻላል።
 • ሠርግ ለማካሄድ በአምስት ሰዎች ብቻ ተወስንኗል (ሙሽሮቹ ተጋቢዎቹ፣ ሁለት ምስክሮችና ጋብቻውን የሚያካሂደው)
 • ቀብር በ10 ሃዘንተኖች ይወሰናል፣ የቀብሩን ሥነስርአት የሚያካሂዱትን ይጨምራል
 • በግል ቤት ውስጥ የሚደረግ ሠርግ ወይም የቀብር ሥነስርአት በቤቱ ውስጥ በሚኖሩት ሰዎች እና በሥነስርአት ፈጻሚዎቹ ብቻ ይሆናል።

የሃይማኖት ሥነስርአቶች እና አምልኮዎች በመስመር ላይ ብቻ ይደረጋሉ።

3ተኛው የትምህርት ክፍለ ጊዜ ሲጀመር ተማሪዎች ትምህርት ቤት ይሄዳሉ።

በእነዚ እገዳ በተጣለባቸው መንደሮች postcodes የምትኖሩና በአሁኑ ጊዜ እረፍት ላይ ከሆናችሁ እረፍታችሁን ቀጥሉ።

COVID-19 የማህበረሰብ ተሳትፎ እናበመንደሮች ውስጥ ምርመራ መጨመር (COVID-19 community engagement and increased testing in suburbs) 

ተጨማሪ የኮሮናቫይረስ መዛመት በታየባቸው መንደሮች፣ መረጃና ምርመራ ለማድረግ የግለሰቦችን ቤቶች እናንኳኳለን

እነዚህ መረጃዎች የት መመርመር እንደሚቻል እና የገንዘብም ሆነ ሌሎች ድጋፎች እንዲሁም መገለል ካለብዎት የመሳሰሉትን ይጨምራል።

በአካባቢዎ ቤት የሚያንኳኩ ካሉ የቴክስት መልእክት ያገኛሉ

ከቤት አንኳኪዎቻችን ጋር ለመነጋገር አስተርጓሚ ካስፈለገዎ ለ TIS National በስልክ ቁጥር 131 450 ይደውሉ።

ተንቀሳቃሽ የምርመራ መኪናዎች , home swab and saliva tests በእነዚህ መንደሮች ይገኛሉ።

ወቅታዊ ግድቦች - በተገደቡ መንደሮች ከሆኑ በስተቀር (Current restrictions – unless you are in a restricted postcode)

 • እጅዎን ይታጠቡ፣ ሲያስነጥሱ ወይም ሲያስሉ አፍዎን እና አፈንጫዎን ይሸፍኑ እንዲሁም ከሌሎች ሰዎች ጋር የሚኖርዎትን የ 1.5 ሜትር የደህንነት ርቀት ይጠብቁ። 
 • የህመም ስሜት ካለዎት፤ እቤትዎ ይቆዩ። ቤተሰብዎን አይጎብኙ ወይም ወደ ሥራ አይሂዱ።
 • የኮሮና ቫይርስ coronavirus ምልክቶች ከተሰማዎት መመርመር አለብዎት። 
 • የሚችሉ ከሆነ እቤትዎ ሆነው መሥራትዎን ይቀጥሉ። 
 • ጓደኞችዎን ወይም ቤተሰብዎን የሚጎበኙ ከሆነ ርቀትዎን መጠበቅ ይኖርብዎታል – መጨባብጥ እና መተቃቀፍ  አይቻልም። ይህም የሚወዷቸውን ሰዎች ደህንነት ይጠብቃል።
 • ሁኔታው ከተቀየረ ዋናው የጤና መኮንን (Chief Health Officer)  ገደቦችን ሊለውጣቸው ይችላል።. 

ከእሁድ ቀን 21 ሰኔ/June 2020ዓ.ም ከሰዓት 11:59 ፒ. ኤም ጀምሮ አንዳንድ ግደባዎች ተለውጠዋል። አንዳንዶቹ የታወጁት ግደባዎች ደግሞ እንዲዘገዩ ተደርገዋል ወይም ሊሰበሰቡ የሚችሉት የሰዎች ቁጥር ተቀይሯል። እነዚህ ልውጦች የተደረጉበት ምክንያት በቪክቶሪያ በኮሮናቫይረስ የተያዙት ሰዎች ቁጥር ስለጨመረ ነው። 

ከቀን 22 ሰኔ/June ጀምሮ፣ ከ 5 ሰዎች በላይ:

 • ቤትዎን መጎብኘት አይችሉም። 

ከቀን 22 ሰኔ/June ጀምሮ፣ እስከ 10 ሰዎች:

 • ውጭም ሆነ ውስጥ መሰብሰብ ይችላሉ።

ከቀን 22 ሰኔ/June ጀምሮ እስከ 20 ሰዎች:

 • ወደ ሬስቶራንት፣ ካፌ፣ መጠጥ ቤት ወይም ባር መሄድ ይችላሉ፣ በእያንዳንዱ ክፍል እስከ 20 ሰው። የአልኮል መጠጥ ያለምግብ ማቅረብ ይቻላል፣ ይሁን እንጂ ሁሉም ደንበኞች በጠረጴዛ ዙሪያ መቀመጥ አለባቸው። ከፍተኛው የቡድን ቁጥር10 ሰዎች ነው።
 • ውጭም ሆነ ውስጥ ስፖርት ወይም ጅምናስቲክ መሥራት ይቻላል። የስፖርት መሥሪያ  እና የዋና ቦታዎችን ጨምሮ፣ ወደ ስፖርት ማእከሎች መሄድ ይቻላል። በየክፍሎቹ ተሰብስበው የአካል እንቅስቃሴ የሚያደርጉት ስዎች ቁጥር ከ10 መብለጥ የለበትም። 
 • ወደ ማምለኪያ ስፍራዎች ወይም አነስተኛ የሃይማኖት ስርዓቶች ይሂዱ፤ ስርዓቱን የሚያዘጋጁትን ሰዎች ጨምሮ።
 • ወደ ቁንጅና ስላሎን ወይም ስፓ ወይም አካልን ማጠየሚያ፣ ጸጉር መንቀያ፣ ጥፍር ማስተካለያ፣ ንቅሳት ወይም የመታሻ ሳሎኖች ይሂዱ።
 • የጋብቻ ስነስርዓት ፈጻሚዎችን እና ተጋቢዎችን ጨምሮ፣ ወደ ሰርግ ቤት ይሂዱ። ስነስርዓቱ በግል ቤት የሚደረግ ከሆነ፣ 5 ታዳሚዎች፣ የጋብቻ ስነስርአት ፈጻሚዎች እና ተጋቢዎች ብቻ መገኘት ይችላሉ። 
 • ወደ የባህልና ማሕበራዊ ማእከላት፣ ቤተ መጻሕፍት ወይም የማህረሰብ ክበቦች ይሂዱ።
 • በቤት ውስጥ ወደሚገኙ የስእል አዳራሾች፣ ቤተ መዘክሮች፣ ሲኒማ ቤቶች፤ የትያትር ቤቶች፣ ታሪካዊ ቦታዎች፣ በውጭ በሚገኙ የመዝናኛ መናፈሻዎች ወይም ወደ መካነ አራዎቶች መሄድ ይቻላል። 
 • ጉዞ፣ ቪክቶሪያ ውስጥ ብቻ የሚያደርጉት ከሆነ፣ ሆቴሎች መከራየት እና/ወይም ወደ መዝናኛ ሰፈር መጓዝ ይችላሉ።. 

እሰክ 50 ሰዎች ቀብር ስነስርዓት ላይ መገኘት ይችላሉ (ውጭም፣ እቤት ውስጥም) ቀብሩን የሚያስተናግደውን ሰውና የቀብር ቤቱ ሠርራተኞችን ጨምሮ። የቀብሩ ስነስርዓት በግል ቤት የሚደረግ ከሆነ፣ 5 ሃዘንተኞች ብቻ መገኘት ይችላሉ። 

የማህበረሰብ እስፖርት: 18 ዓመት ወይም ከዚያ በታች ለሆኑ ሰዎች፣ ንክኪ ያለበት የስፖርትልምምድ ሊጀምሩ ይችላሉ። በሁሉም የእድሜ ክልል ያሉ ሰዎች ንክኪ የሌለው የስፖርት ውድድር  መጀመር ይችላሉ።

መጠንቀቅ እንዳለብዎት ያስታውሱ፣ ሁሉንም ባገናዘበ መልኩ እራስዎን ይጠብቁ። እቤትዎ ሆነው መሥራት ከቻሉ፣ እቤትዎ ሆነው መሥራት አለብዎት። እራስዎን ውጭ መውጣት ለሚያስፈልግዎ ጉዳይ ብቻ ይወስኑ።

የቪክቶሪያ መንግሥት ለሚገባቸው የቪክቶሪያ ሠራተኞች፣ የኮሮናቫይረስ ለተገኘባችው ወይም በሽታው በእርግጥ ከያዛቸው ጋር ንክኪ ላደረጉ ሰዎች፣ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚከፈል፣ የ$1,500 የድጋፍ ክፍያ ያደርጋል። ለተጨማሪ መረጃ ለኮሮና ቫይረስ የድጋፍ መስመር በስልክ ቁጥር 1800 675 398 (በቀን 24 ሰዓት) ይደውሉ። አስተርጓሚ ከፈለጉ TIS National ን በ131 450 ደውለው ይጠይቁ።

ግብአቶች (Resources)

እባክዎን ከታች የተዘረዘሩትን ቁሳቁሶች ይጠቀሙ እንዲሁም ለማሀበረሰብዎ በኢሜል፣ በማህበራዊ መገናኛዎች ወይም በማህበራዊ መረቦች ያካፍሉ።